Press Release for the Upcoming Weyane Instigated "Kimant Referendum"

ቅማንትን እና ዐማራን ለመለያየት የሚደረገውን ሴራ  በመቃወም የዐማራ ድርጅቶች እና ማህበራት ያወጡት የጋራ  መግለጫ!

የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግምባር(ትህነግ)  ቁንጮ  በመለስ ዜናዊ ፥  በአባይ ፀሐዬና በስብሃት  ነጋ በ1968  ተረቆ በትህነግ   ማኒፌስቶ  በጉልህ ተቀምጦ የኖረውና  ትህነግ    ሥልጣን ከጨበጠም  በሗላ ያልተወው  መሪ ሃሳብ “ዐማራ የትግራይ ህዝብ ታሪካዊ ጠላት ነው”  የሚል ሲሆን ይህንን መርህ ተከትሎ ይህ ፋሽስታዊ  ድርጅት  የዐማራን ሕዝብ ሲገድል ፥ ሲያፈናቅል ፥  ለብሽታ ለረሃብና ለእርዛት ሲዳርግ ፥  እንዲሁም   ወላድ አንስቶቻችንን በመድሃኒት ሲያመክን እነሆ  አራት አሥርት አመታት ተቆጥረዋል::

ትህነግ ዐማራን ከማጥፋት አላማው  በተጓዳኝ የትግራይ ሪፖብሊክ ሃገረ መንግስት ምስረታውን በአጣዳፊ መልክ እየገፋበትም ይገኛል:: ለዚህም  አላማው  የተለያዩ ዘዴዎችን ሲጠቀም  የኖረ ሲሆን አሁን ደግሞ የቅማንት ሕዝበ ውሳኔ በሚል አዲስ አሻጥር ለሆዳቸው  ያደሩ ጥቂት የቅማንት ሰዎችን አሰባስቦ በማደራጀት ዐማራን ከተለያዩ ወረዳዎች ለማፅዳትና ቦታውንም ለመቆጣጠር ደፋ ቀና እያለ ይገኛል::

ትህነግ በመላ ኢትዮጵያ ዐማራን ርስት-አልባ ለማድረግ የተጠቀመበት ዘዴ  በሃገሪቱ  የሚኖሩትን ብሄር ብሄረሰቦች  መርዛማ የጥላቻ  ትምህርት  በማጋትና ለዕኩይ  ተግባሩ  ተባባሪ  እንዲሆኑ በማድረግ ሲሆን ይህንን ተከትሎ   የዐማራ ሕዝብ  ከሃገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች በግፍ  እየተገደለና  ንብረቱን  እየተቀማ እንዲፈናቀልና እንዲባረር ተደርጓል:: ትህነግ በወልቃይት ጠገዴ  እና በተቀረው  የሃገሪቱ  "ክልሎች" ስልጣን ከጨበጠ ግዜ ጀምሮ ሲሰራበት የነበረውን ይህን ፋሺስታዊ አሰራር አሁን ደግሞ በተመሳሳይ መንገድ  በጎንደር  ውስጥ  ጥቂት ለሆዳቸው  ያደሩ ቅማንቶችን በመሰብሰብ  እና በማደራጀት መስከረም  7 ቀን 2010 ዓ.ም  በቀጠረው   ሕዝበ ውሳኔ የራስ አስተዳደር በሚል ሰበብ  ከተለያዩ ቀበሌዎች  እና  ወረዳዎች ዐማራን ለመፍጀት እና  ለማፈናቀል ዝግጅቱን አጠናቋል::

በትህነግ ታሪክ ውስጥ  ህዘበ-ውሳኔ ወይንም   ምርጫ   አደገኛ ተንኮልን የተላበሰ  ማደናገርያ ስለመሆኑ ምንም  ትንታኔ እንደማያስፈልገው  ድፍን የሃገሪቱ  ሕዝብ ያውቀዋል:: ፀረ-ሕዝብ  የሆው   ትህነግም በታሪኩ ለተሻረካቸው  ቡድኖችም  ሆነ ሃገራት  ታማኝ  አለመሆኑ የገዛ ታሪኩ  ምስክር ነው:: ለምሳሌ ትህነግ ከሻዓብያም  ሆነ ከኦነግ  እንዲሁም  ከኦብነግ  ጋር  የገባውን ቃል ኪዳን ግዜ ጠብቆ በመካድ የተሻረኩትን በሙሉ ለማጥፋት ያልተኛና የማይተኛ መሆኑ አሁንም  የድርጅቱ አጭር የሕይወት ታሪክ ምስክር ነው:: በሕዝበ ውሳኔ ሰበብና መርዛማ  በሆኑ የተለያዩ ትምህርቶች  ቅማንትን ከወገኑ  ከዐማራ ለመለየት የተጠራው  ሕዝበ-ውሳኔም   ትህነግ ስለሚመኘው  የትግራይ  ሪፓብሊክ  ሕልም  ተግባራዊ ለማድረግ  እንዲጠቅም ተብሎ  የተጠነሰሰ  ስለመሆኑ የቅማንት ሕዝብ ሊረዳው ይገባል::  የግዜውን አስከፊነት   እና   ትህነግ    ይዞት  የመጣውን መርዝ አዘል ተልዕኮ ጉዳዩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሚመለከታቸው  ለቅማንት  ሕዝብ  ፥  ለዐማራ  ሕዝብ ፥  እና   ይህ ተንኮል አፍንጫው   ስር ሲደረግ ምንም  ለማድረግ ዝግጁ  ላልሆኑት  ከተራ  እስከ ከፍተኛ አመራር ላይ ላሉት ለብአዴን አመራሮች  በሙሉ  ይህንን  መልዕክት  አስተላልፈናል::

የቅማንት ሕዝብ ሆይ

የቅማንት ህዝብ  ከዐማራ  ህዝብ  ጋር ለሺዎች አመታት አብሮ ኖሯል፤ ተጋብቷል፤ ተዋልዷል፤ ለአንድ አገር ሞቷል። የቅማንት ህዝብ  ቋንቋዬና ባህሌ  ሊጠፉ ነው፤ በቂ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል በማለት ጥያቈ ቢያቀርብ  ትክክለኛ ነው። ፍትህና ፍርድን ከትህነግ መጠበቅና መሻት አልፎም  ከትህነግ  ጋር ቡድን ሰርቶ  ዐማራን ለማጥቃት  መነሳት ግን ዋጋ የሚያስከፍልና ወደፊት ሰላምን የሚነሳ ትልቅ ሥህተት ነው:: ትህነግ    በመላ ሃገሪቱ  የተጠላ ዘረኛና አውዳሚ  ድርጅት  መሆኑ  እየታወቀ  ቅማንትን እንወክላለን የሚሉ  ግለሰቦች  በዚሁ  ድርጅት  መቀሌ  ውስጥ  ቢሮ ተሰጥቷቸው  የመከፋፈል  መርዛማ  ሥራ  ሲሰሩ ለቅማንት  ሕዝብ  ታስቦ እንዳልሆነ የቅማንት  ሕዝብ  ሊረዳው  ይገባል::

የወያኔ የክልልና ዞን አወቃቅር አጥር አጥሮ “ይሄ የኔ ነው” አትድረስብኝ አትምጣብኝ የሚል አስተሳስበን በመፍጠር በሃገሪቱ ውስጥ  በየቦታው  ግጭት እና   የሕይወት መጥፋትን እያስከተለ እንደመጣ  ዘወትር የሚነገር  ነው:: ይህም  "ከፋፍለህ ግዛ" ተብሎ  በቅኝ ገዢዎች  ሕዝብን ከፋፍሎ እያናቆረ  የሚያኖር እና   ገዢውን ግን የሚያበለጽግ  አሰራር ስለመሆኑ  ለቅማንት ሕዝብ  የተሰወረ ሊሆን  አይገባም:: ትህነግ ለቅማንት  ልሰጠው  ነው  የሚለው የዞን አጥር  ዐማራን ከአካባቢው  ከማጽዳት ባሻገር  ቅማንትንም  ታጥሮ  ከቦታው  ለዝንተአለም  እንዳይወጣ  ሊያረገው  እንደሚችል የቅማንት ሕዝብ  ሊረዳው ይገባል:: ትህነግ  እና  አንዳንድ  ቅጥረኞቹ  እንዳለሙት  የቅማንት  ዞን ከተፈጠረ  ቅማንት  የሚሰራበትን  እና   የሚኖርበትን ወረዳና ቀበሌ  ለቆ  እንዳይወጣና  ከወጣም  ፀጉረ-ልውጥና ባይተዋር  እንዲሆኑ ሊያደርጋቸው  እንደሚችል ሊታወቅም ይገባል:: ይህም  ራስን በራስ ከማጥፋት ተለይቶ አያታይም።

ትህነግ እንኩዋን  በቀበሌና በወረዳ ደረጃ  በሃገር  መዋቅር ውስጥ  ሳይቀር  የትግሬን  የበላይነት ማንገሱ  እየታወቀ  ቅማንት ብሎ  በሚፈጥረው  አስተዳደር  ውስጥም  የትግሬ  የበላይነት  አይነግስም ብሎ  ማሰብ  እና መመኘት  ሞኝነት  እና   አርቆ አለማሰብም  ነው:: ይህ ብቻ ሳይሆን ዐማራን በማፈናቀል ቅማንት  እና  ዐማራን መቆምያ ወደሌለው  ጠላትነት  እና  ደም መቃባት ለማድረስ የተጠነሰሰ ሴራ መሆኑን ሁሉም  ቅማንት  ሊረዳው  ይገባል:: ይህ የትህነግ    ሴራ  በአካባቢው  ለሚኖረው የቅማንት  እና  የዐማራ ሕዝብ  ከትውልድ  ወደ  ትውልድ  የሚወርድ  አውዳሚ  የሆነ የጸብ  ግድግዳን ሊፈጥር እንደሚችል ከወዲሁ አናሳስባለን::

የቅማንት ሕዝብ  በታሪኩ  ሊወግን የሚገባው  ለዘመናት  አብሮት ከኖረው  ከተጋባው   እና  ከተዋለደው የዐማራ ሕዝብ  ጋር ነው:: የትህነግን “ትግራይ የሚባል ሃገር” ህልም   ተግባራዊ  ለማድረግ  የቅማንት  ልጅ እንደ  መሰውያ ሆኖ እንዲቀርብ የተደረገን  ድብቅ  ሴራ  የቅማንት  ሕዝብ  እንቢ  ሊለው  ይገባል:: ለአንድ  ማህበረሰብ  ሰላም   እና   ብልጽግና ወሳኙ አካባቢያዊ  ሰላም  ሲሆን ቅማንትን  ወደ ማያልቅ  እና   ወደ ማይባራ  መተላለቅ  በመክተት  የሚገኝ  ለትውልድ  የሚተርፍ ሰላም  እና   ብልጽግና አይኖርም:: ትህነግን  እንደ  ሸሪክ  ወስዶ  ዐማራ  ላይ  ማበር  ከቅማንት  ሕዝብ  አኩሪ  ባህል  እና ሰው   አክባሪነት ጋር አብሮ አይሄድም::ስለዚህ ይህንን  ተንኮል  አዘል  ሴራ  የቅማንት  ሕዝብ  አልቀበልም  ሊል  ይገባል::

ለተከበርከው ደጉ  የቅማንት ሕዝብ እዚህ ላይ ማወቅ ያለብህ በትግራይም ሆነ በኦሮሚያ ተብሎ በሚጠራው  "ክልል"  ውስጥ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩ እንደሆነ ቢታወቅም  የትግራይም  ሆነ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መተዳደሪያ ደመብ የሚጠቅሰው የትግራይ ሕዝብ ወይም የኦሮሞ ሕዝብ ብሎ እንጂ  የትግራይ ሕዝቦች   ወይም የኦሮሞ  ሕዝቦች ብሎ አይጠቅስም። በአንጻሩ የዐማራ "ክልል"  ብሎ ወያኔ በሚጠራው አካባቢ  በሃዘን ፥ በደስታ ፥ በጋብቻ ፥ በሃየማኖት   እና በባህል አንድ ሆኖ ለሦሥት እሺ ዓመታት አብሮ የኖረውን  ማሕበረሰብ  ሕዝቦች እያለ ለመለያየት የማይፈነቅሉት ጉድጓድ የለም። ይሄም አልበቃው ብሎ በትግራይ ወይም በኦሮሚያ  "ክልል " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ብሔርን ማዕከል  ያደረገ  ዞን የሚባል ነገር ሳይኖር በዐማራ "ክልል" ብቻ  ብሔርን ምዕከል ያደረገ ዞን እየፈጠሩ የዐማራውን   እና የቅማንትን  መሬት ለመንጠቅ የታሰበ ሴራ እንደሆነ የቅማንት  ሕዝብ ልብ ሊል ይገባል።  በሃገራችን የማንነት ጥያቄ የሚከበር ቢሆን ኖሮ የትግራይ "ክልል" ተብሎ በሚጠራው  አስተዳደር ውስጥ የኩናማ ዞን እና የዐማራ ዞን በተፈጠረ ነበር። በተመሳሳይ ሁናቴ  የኦሮሚያ "ክልል" ተብሎ በሚጠራው  አስተዳደር ውስጥ  የዐማራ እና የሌሎችም ብሔር  ብሔረሰቦች ዞን በተፈጠረላቸው ነበር።  ነገር ግን የወያኔ የመጨረሻ አላማ ዐማራን ማጥፋት እንጂ የሕብረ ብሔር የማንነት ጥያቄ በሃገራችን ማስፈን እንዳልሆን ደጉ የቅማንት ሕዝብ ሊገነዘብ ይገባል::

የቅማንት  ሕዝብ  ሆይ፥  ይህ መልዕክት ለዘመናት አብሮህ ከኖረ  እና   ከተዋለደህ የዐማራ ሕዝብ የተላለፈ መልዕክት ነው:: ትህነግ    በማር  የተለወሰ  መጥፊያ  መርዝ  ይዞልህ መጥቷልና የወያኔ ቁማር መጫወቻ  ጠጠር አትሁን፤ ዐማራ ወንደምህን ለመግደያ ዱላ ለወያኔ አታቅብል። ወያኔን ተማምነህ የታላቁን የዐማራ ህዝብ አይን አትጠንቁል፤ ጀግናው  የዐማራ ህዝብ ወያኔን የታሪክ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ የሚከትበት ጊዜ ቅርብ ነውና። ከጥንት ጊዜ ጀምሮ  ከዐማራ  ወገንህ ጋር በክፉዉም  ሆነ በደጉም አብረህ ስትወድቅ እና  ስትነሳ ለሺዎች ዓመታት ዘልቀሃል። አገር ስትወረር ከዐማራው  ወገንህ ጋር አብረህ ጀብድ  ሰርተህ፣ አብረህ ተሸልመህ  ወግና  ማዕረግ ደርሶሃል። ዛሬ ግን ትህነግ  የመጥፊያ መንገድህን አስምሮልሃል። ይህን ወደ ኋላ መለስ ብሎ የመቃኘት  እና   ሰክን ብሎ  ይህን የተንኮል እቅድ ማክሸፍ ያንተም  ዋና ተግባር መሆን አለበት። የአዛውንቶችህ አርቆ አሳቢነት የሚፈተንበት ጊዜ አሁን ነው።  ብታምንም  ባታምንም  የወደፊቱ እጣ ፈንታህ ያለው  ከትህነግ    ጋር ሳይሆን በውስጡ ከምትኖረው  ከሰፊው  ዐማራ  ሕዝብ ጋር ነው። አሁን የምትሰራው  ይቅር የማይባል ዘለዓለማዊና ታሪካዊ ስህተት  የቀሪውን ትውልድ  እጣ ፈንታ  ይወስናል። እንድታስብበት ጥያቄ  ቀርቦልሃል።

ሰፊው የዐማራ ሕዝብ ሆይ

ሰሞኑን በሃገር ውስጥ  እና በዉጭ  ያለውን መላውን የዐማራ ሕዝብ  ከመቸውም  የበለጠ  ያስቆጣ  ጉዳይ ተከስቷል። ይኸውም፣ በትህነግ    ለረጅም  ጊዜ ታቅዶ አሁን በመተግበር ላይ ያለው ዐማራን የማጥፋት ዘመቻ  በቅማንት  ሥም  አዲስ ምዕራፍ  ውስጥ   ገብቷል። የጎንደር  ዐማራ ሕዝብ  ጋር እስከ  ቅርብ ዓመታት ድረስ ለሺዎች ዓመታት በሰላም  ይኖር የነበረውን የቅማንትን ሕዝብ  የጠቀመ  መስሎ   ትህነግ     ቅማንትን በዐማራ ላይ  በማንነት ጥያቄ ሥም  በማስነሳት የዐማራውን መሬት  ነጥቆ "ለቅማንት ልዩ ዞን"  ብሎ  ለመውሰድ  የፊታችን መስከረም  7 ቀን 2010 ዓ.ም  ሕዝበ ዉሳኔ (referendum) ሊያደርግ ወስኗል። የዚህ እቅድ ዋና ግብ የቅማንትን ሕዝብ ለመጥቀም  ተብሎ ሳይሆን ለሁለት ዋና ዋና ዓላማዎች ነው። የመጀመሪያው   የቅርቡ  ዓላማ  ለዐማራ  ከጉያው  ውስጥ  ጠላት  አስነስቶ  እንዲታመስ በማድረግ  የቅማንት እና የዐማራን ሕዝብ ደም  እንዲቃቡ  እና ጦርነት  እንዲነሳ በማድረግ  የወልቃይትን የዐማራ  የማንነት ጥያቄ ለማኮላሸት  እና ጊዜ ለመግዛት ሲሆን፣ ሁለተኛውና የሩቁ ግብ  ደግሞ ለቅማንት እሰጣለሁ  ባለው  ዞን ውስጥ  የሚኖረውን  የዐማራ ሕዝብ ከመሬቱ  እየነቀለ  ካስወጣ  በኋላ በምትኩ  በወልቃይት  እንዳደረገው   በመቶ ሺህዎች  የሚቆጠሩ  ትግሬዎችን አምጥቶ  በማስፈርና የቅማንትንም   ሕዝብ  ማንነት  በግድ  ወደ ትግሬነት  በመቀየር መሬቱን ወደ ትግራይ ለማካለልም ነው::

ይህ ከላይ የተገለፀው  የትህነግ    አካሄድ  በቅማንት ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን ከጎጃም  ዐማራ ሕዝብ  ጋር አብረው  የሚኖሩትን የአገው  እና  የወይጦን አናሳ ነገዶችንም  እንዲሁ በማስነሳሳት በማንነት ጥያቄ ሥም  የዐማራን መሬት መንጠቅ እና  ወደፊት ዐማራ እንኳን የሚኖርበት የሚረግጠው  መሬት እንዳይኖረው ለማድረግም  ነው::


ውድ  የዐማራ ሕዝብ ሆይ ትህነግ    ወደ ደደቢት ጫካ  ከገባ ከ1967 ዓ.ም  ጀምሮ በቁጥር አንድ ጠላትነት ተፈርጀህ የታቀደልህ የጥፋት ውርጅብኝ በብዙ ሚሊዮኖችም  ከተጨፈጨፍክ፣ ከተሰደድክ፣ ቤት ንብረት እንዳይኖርህ፣ ሰርተህ እንዳትበላ ተደርጎ አይንህ እያዬ ቤተሰብህ ተበትኖ ልጆችህ ወደ ለማኝነት  እና ሴትኛ አዳሪነት ከተቀየሩም  በኋላ የሚያበቃ አልሆነም። ጥቃትህ በአገርህ ላይ እንዳትኖር "ይህ ያንተ ግዛት አይደለም፣ ንብረትክን ጥለህ ጥፋ" እየተባልክ በመፈናቀልህ  እና ለአፅመ  ርስትህ ተቆርሶ ማንነትህን ቀይር በመባልህም  አላበቃም። እነሆ አሁን ጭራሽ ይባስ ብሎ ተቀናንሶ በተበጀልህም ጠባብ  በረት ውስ ጥ እንኳን በሰቆቃ ለመኖር እንኳ  አልተፈቀደልህም።

ውድ የዐማራ ሕዝብ  ሆይ እስካሁን እንደ ዉቅያኖስ በሰፋው  ትዕግስትህ  ይቅር ስትልና በደልህን ለአምላክ ስትሰጥ  ቆይተሃል። አሁን ግን ፅዋው  ሞልቶ፣ ፈሥሦ  ተንቀሃል። ከዚህ በኋላ የሚያጓጓህ አንዳችህ ነገር የለም። ይህን ሁኔታ ባስቸኳይ ካላስቆምክ ከዚህ በኋላ የሚቀርህ ሞትና መሰደድ ብቻ ነው።

ብዓዴን ውስጥ ላላችሁ ዐማሮች

የብአዴን   ማዕከላዊ ኮሚቴ አመራር አባላት  ፥  የዐማራ ክልላዊ መንግስት ካብኔ አባላት ፥   በኢፌድሪ ፓርላማ  ዐማራን ለሚዎክሉት  ለ138  የፓርላማ  አባላት  ፥ለዐማራ "ክልል"  ምክር ቤት አባላት ፥ የወረዳ ፥  የዞን  እና የቀበሌ አመራር አካላት እና አባላት  በዐማራ ህዝብ ላይ ትህነግ  የሚደረገውን ይህንን ስውር ሴራ በመደገፍ በዐማራ ህዝብ ታሪክ ውስጥ  ለራሳችሁ፣ ለልጆቻቸሁና ለቀሪ የሥጋ ዘመዶቻቸሁ ከፍተኛ የበቀል አደጋ የሚያስከትልን ይህንን ተግባር ባላቸሁ ሥልጣን ሁሉ እንድትቃወሙ እና እንድታስቆሙ እየጠየቅን ፤ ይህንን የሕዝብ  ጥሪ ረግጣችሁ  እና   ንቃችሁ በሕውሃት መሰሪ ሴራ የተሳተፋችሁ አመራሮች ሙሉ ሃላፊነቱን የምትወስዱ ሲሆን ወደፊት ለሚከተለው  ማንኛውም  ጥፋት ግምባር ቀደም  ተጠያቂ ከመሆን የማትድኑ መሆኑን  እናሳስባለን።

ከዚህ በታች ሥማችሁን የዘረዘርናችሁ የትህነግን ትዕዛዝ በዐማራ ሕዝብ ላይ ያለምንም ተቃውሞ የምታስፈጽሙ የዐማራ ክልላዊ መንግስት የካቢኔ አባላት እንዲሁም ሥማችሁን እዚህ ያልተጠቀሰና  ወደፊት ይፋ የምናደርጋችሁ  ግለሰቦች ይህንን ታሪክና ሕዝብ ይቅር የማይለውን ወንጀል ተባባሪ ከመሆን እንድትቆጠቡና ራሳችሁንም  እንድታገልሉ እናሳስባለን:: ወንዝና ድንበር አቁዋርጦ  የባርነት ቀንበርን በሕዝባችን ላይ ጭኖ እያዋረደን ያለን ጠላት ከማገልገል የማትቆጠቡ ከሆነ ግን በናንተ ፥በቤተሰቦቻችሁ እንዲሁም በልጆቻችሁ እና በልጅ ልጆቻችሁ ለሚደርሰው  የወደፊት ጭንቅ ቀን ተጠያቂው ራሳችሁ ናቸሁ:: በዚህ  የቅማንት  ዐማራ ሕዝበ-ውሳኔ በቀጥታ  ተሳታፊ የሆኑ የኮሚቴ አባላት  በተመሳሳይ  ለጊዜአዊ  ጥቅም  ብለው  ዘላለማዊ  የህዝብ  ጠላት  ለራሳችሁና ለቤተሰቦቻቸሁ አንዳትተክሉ  እያሳሰብን ባስቸኳይ  ከአባልነት  እራሳቸውን እንድታገሉ  እንጠይቃለን ።

አቶ ይልቃል ከፋለ አስረስ (ለትምህርት ቢሮ ሃላፊ)
ዶ/ር አበባው ገበየሁ ወርቁ (ለጤና ጥበቃ ቢሮ ሃላፊ)
አቶ ሞላ ፈጠነ ደሴ (ለውሃ መስኖ እና ኢነርጅ ቢሮ ሃላፊ)
አቶ ፀጋ አራጌ ትኩየ (ለመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ)
አቶ ፍስሃ ወልደ ሰንበት (ለአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ)
ዶ/ር ጥላሁን መሃሪ አንተነህ (ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ)
ዶ/ር ሂሩት ካሳ ወንድም (ለባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ)
አቶ ሞላ ጀንበሬ አለምነህ (ለሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ)
አቶ መሀመድ አብዱ- ዐማራ "ክልል"  ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
ዶክተር በላይነህ አየለ-አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ቢሮ ሀላፊ
አቶ ላቀ አያሌው (ለዐማራ "ክልል"  ቴክኒክ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሃላፊ)

ትህነግ እና አጋሩ ብዐዴን የጀመሩት ተንኮል በምን እንደሚጠናቀቅ ለማወቅ ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልግም:: ከዚህ በፊትም ኢትዮጵያን እንደ ቅርጫ ስጋ ነፃ አውጪ ነን ባዮቹ ኤህነግ/ትህነግ/ኦነግ በ "ክልል" ሲከፋፍሉ: ዛሬ ብዐዴን ተብዬው ድርጅት መሪዎች  ዐማራውን ሁሉም ወስዶ የተረፈውን እንደ በሬ ግንባር የጠበበ  ዐማራ "ክልል" የሚል ማስቀረታቸው አልበቃ ብሎ: ሌሎች "ክልል" ተብዬዎች ላይ ያልተደረገ  የ ዐማራ "ክልል" ያሉትን የተለያየ "ልዩ ዞኖች" እንዲፈጠር እንዳደረጉ እናውቃለን:: በቅርብም ዐማራው ማንነቴ በግድ እንዲጠፋ ተደርጓል: በታሪክ ትግራይ ከተከዜ አልፎ ሳያውቅ በግድ ትግራይ" ክልል" ተካተን ዐማራነታችን እንዲጠፋ እየተደረገ ስለሆነ: ዐማራነታችን ይመለስ ብሎ  ዐማራው  የሞት ሽረት ትግል ሲያደርግ: ብዐዴን ተብዬው ተጨማሪ መሬት  ለትግራይ " ክልል" እንደሰጠ እናውቃለን:: በተመሳሳይም የቅማንት ጉዳይ በሚል: የተጀመረው ዐማራን የመከፋፈል ተንኮል የቅማንት እና የዐማራ ህዝብ በጋራ ሃይ ካላልናቸው በስተቀር በግድ በዐማራ እና በቅማንት መካከል ያልነበረ ድንበር ከመስራት እና እርስ በእራሳቸው ዐማራ እና ቅማንትን በማጣላት: ዐማራውን መግደል እና ማፈናቀል መጀመራቸው ላይቀር ይችላል:: እኛ ግን የምንላችሁ ቢመሽም ይነጋል: ሊነጋ ሲል ይጨልማል ነው እና ዐማራ የአባቶቹን ርስት ሳያስመልስ መቼም አይተኛም:: ዐማራ ሳይወከል ወይንም በእንግዴልጁ ብአዴን የተፈፁሙ ስምምነቶች  ሁሉ ውድቅ ሆነው ሁሉም ነገር በቅርብ ወደቀደመ ቦታው ይመለሳል:: ነገሮች መስተካከላቸው ላይቀር: ይልቅስ ለትውልድ  የሚተርፍ  ደም  ህዝቡን ባታቃቡት ይሻላል: በተለይ የቅማንት ህዝብ: ትህነግን ማመን ከአጋም እሾህ እንደመጠጋት መሆኑን ተደጋጋሚ የክህደት ተግባራቸውን አይቶ መረዳት ይቻላልና: ከዐማራው ጋር እንደሁሌው  ድንበር ሳይበጅ አብሮ መኖሩን እና መከበር ይገባዋል የምትሉትን ባህልም ይሁን ቋንቋ ማስጠበቁ ይሻላችኃል::

የቅማንት  ህዝብ ሆይ አይነጋ መስሏት አይነት እንዳይሆን ወዳጅ መስሎ ሁሌም ጠላት ከሆነው ትህነግ ጋር ወግነህ ለዘመናት ተቀላቅሎ አብሮ ከኖረው ዐማራ ወገንህ ጋር ደም አትቃባ::

የዐማራ ህዝብ ሆይ ተነስ መብትህን አስጠብቅ::

ጆሮ ያለው ይስማ!!! 

ከላይ የወጣውን የጋራ መግለጫ ያወጡት የዐማራ ድርጅቶች  እና ማሕበራት ዝርዝር

  1. ሞረሽ  ወገኔ  የዐማራ ድርጅት
  2. የዐማራ ሕልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት
  3. ቤተ ዐማራ  ድርጅት
  4. አምባ የዐማራ ባለሞያዎች ማሕበር
  5. ሲያትል  የዐማራ ማሕበር 
  6. ዲሲ የዐማራ ማሕበር
  7. ቦስተን የዐማራ ማሕበር 
  8. ሳንዲ ያጎ  የዐማራ ማሕበር
  9. ዳላስ  የዐማራ ማሕበር
  10. አትላንታ  የዐማራ ማሕበር