መንግሥት የፈጠረው መንግሥት አልባነት

                                 መንግሥት የፈጠረው መንግሥት አልባነት

                                                    ማክሰኞ፤ ግንቦት ፳፱ ቀን፣ ፳፻፲፭ ዓ. ም.

አሁን በኢትዮጵያ ያለው የአክራሪ ኦሮሞዎች ፅንፈኛ የገዢ ቡድን፤ አገራችንን መንግሥት አልባ አድርጎ፤ ወደ የማትመለስበት አዘቅት ውስት ሊከታት እያንደረደራት ነው። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በተደረገው የፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት፤ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ነኝ ብሎ አገር የወረረው ፀረ-ኢትዮጵያ ቡድን ትጥቁን እንዲፈታ ስምምነት ተደርሶ እያለ፣ ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጋር በመተባበር የአካባቢውን ሕዝብ በመጨፍጨፍ ላይ ያለው የኦሮሞ ልዩ ኃይል እንደታጠቀ እያለ፤ ኢትዮጵያን የታደጋትን፣ በራሱ ትጥቅና ስንቅ ቤቱን ትቶ ሕይወቱን የሠጠውን ፋኖና፤ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት፤ የአክራሪ ኦሮሞዎች ገዢ ቡድን በአማራ ክልል ዘምቷል። ይህ ዘመቻ ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ገጥሞታል። ይሄን ያደረገ መንግሥት፤ የሕዝቡ የበላይ ነኝ ብሎ፤ በጉልበቱ ለመግዛት የወሰነ ነው። እናም ሕዝቡ በዚህ ገዢ ቡድን ላይ እምነቱን አጥቷል። ያሰራቸው፣ የሰወራቸው፣ ያፈናቸው የአማራ ልጆች ቁጥሩ እያሻቀበ ነው። አማራዎች ሕልውናቸውን ለመጠበቅ፤ በያሉበት በየመንደሩ ተደራጅተው እየተረባረቡ ናቸው። ይህ የሕልውና ትግል፤ አማራዎች በያለንበት፤ ትግሉ የኛ ነው በማለት፤ በአንድ ላይ እንድንነሳ አስገድዶናል።

ቅዳሜ፣ ግንቦት ፲ ፱ ቀን፣ ፳፻፲፭ ዓ. ም. በውጪ አገር የምንገኝ የዓለም አቀፍ የአማራ ንቅናቄ (ዓየን) አባላት፤ ትልቅ ስብሰባ በማድረግ፤ እየተካሄደ ላለው የአማራዎች የሕልውና ትግል፤ ድርጅታችን በውጪ አገራት ያለው የአማራ እንቅስቃሴው መሪመሆኑን ገልጠናል። በዚህ ስብሰባችን፤ በአማራዎች ላይ ተደጋጋሚ የተለያዩ ጥቃቶች፤ ከበደል አልፈው የዘር መፍጀት ደርጃ የያዙ መሆናቸውን አስፍረናል። ይሄ በአማራዎች ላይ የሚካሄደው የዘር ፍጅት፤ በአንድ ሰዓት፣ በአንድ ቀን፣ በአንድ ጊዜ የተፈጸመ ሳይሆን፤ በሂደት፣ ለረጅም ጊዜ አስበውበት እና ሌሎችን በመመልመል የሃሳቡ ተገዥዎች አድርገው፤ በትንሹ በአንድ አካባቢ ተጀምሮ፤ እየተሞከረና እየተሞረደ፤ ጥልቀቱና ስፋቱ በጊዜ ያደገ፤ ጥላቻና ጥላቻው የፈጠረው የበቀል ስሜት ነው። አናም ለዚህ መልስ፤ አሁን ሰዓቱ በአንድነት ተደራጅቶ፤ ራሱን መጠበቅና፤ ከሌሎች አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን፤ በሥልጣን ላይ ያለውን የአክራሪ ኦሮሞ ፅንፈኛ ገዢ ቡድን፤ ከሥልጣን ማስወገድ መሆኑን አስቀምጠናል። ይህ የአገር አድን ጉዳይ ነው!!!

በአማራዎች ላይ እየደረሰ ያለው፤ በአንድ ግለሰብ ወይንም በአንድ ቡድን፤ በአንድ አካባቢ የተደረገ በደል፤ እናም የአንድ ግለሰብ ወይንም የአንድ ቡድን ችግር አይደለም። በየትም ቦታ በአክራሪው የኦሮሞ ፅንፈኛ ገዢ ቡድን የሚደረገው አማራዎችን የማጥፋት ተልዕኮ፤ በመላ አማራዎች ላይ፤ በአማራነታችን ላይ የታወጀ ዘመቻ ነው። ይህ የመላ አማራዎችን ሕልውና ጥያቄ ያስገባ ዘመቻ ነው። እናም ትክክለኛና በቂ መልስ የሚያገኘው፤ አክራሪውና አገር አጥፊው ቡድን ከሥልጣኑ ሲባረር ብቻ ነው። እናም ለያንዳንዳችን አማራዎች፤ የዚህ ትግል አካል መሆን፤ የሕልውና ግዴታችን ነው። አክራሪው ፅንፈኛ የኦሮሞ ገዥ ቡድን ወድሞ፣ በአንዲት ኢትዮጵያ፤ አማራዎች ሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን፤ በእኩልነትና በአንድነት እንኖራለን!

በሥልጣን ላይ ያለው የአክራሪ ኦሮሞ ፅንፈኛ ገዢ ቡድን፤ በክርስትናና በእስልምና ምዕመናን ላይ የሚያደርገው አረመኔያዊ ተግባር፤ የሃይማኖት ተቋሞች ላይ እያደረገ ያለው የጥፋት ዘመቻ፤ አገሪቱን እና መሠረታዊ የሆኑ አገራዊ ተቋማቶቿን ለማፍረስና አዲስ፤ ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ አገርና መንግሥት ለመመሥረት እንደሆነ ተረድተናል። የዚህ ማሽከርከሪያው፤ አገራቸውን ኢትዮጵያን ወዳድ የሆኑትን አማራዎች ማጥቃትና ሌሎችን አንበርክኮ የአክራሪ ኦሮሞዎች መንግሥት ማቋቋም ስለሆነ፤ ከዚህ የመነጨውን አማራውን ትጥቁን አስፈትቶ ከፖለቲካ ተሳትፎው ማስወጣት ዘመቻ፤ አጥብቀን እናወግዛለን። ሁላችንም በአንድነት ለወገናችን የሕልውና ትግል አጋዥ መሆን ግዴታችን ነው ብለናል። ይህ የአክራሪ ኦሮሞዎች ፅንፈኛ ገዢ ቡድን፤ አገራችንን ኢትዮጵያን ወደማትመለስበት አዘቅት እየነዳት ነው። አሁን በያዘው አገር የማጥፋት ሂደቱ መቀጠል የለበትም!

የወደፊታችን ብሩህ ነው! የሁላችንም የትብብር ዓይኖች ያበራሉና! የሁላችን የትብብር እጆች ይሠራሉና! የሁላችን የትብብር እግሮች ይገፋሉና! የሁላችን የትብብር አእምሮዎች ጨለማውን ይገፋሉና! ይሄን ሁሉ ጥረት የሚበልጥ፣ የሚያቆም፣ የሚቀድም የለም!!! አማራ ራሱን ተከላክሎ፣ ኢትዮጵያን ከአገር ወዳዶች ጋር ተባብሮ ያድናታል! አብሪዎቹና የብሩህነቱ ጥንካሬ ወሳኞቹ እኛ ነን!!!

 

አምባ የህዝብ ግንኙነት ክፍል

ግንቦት ፳፱ ቀን፣ ፳፻፲፭ ዓ. ም

 

 

 

Is Amharic?
More To Read