ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ!

መጠጊያ አጥተው የባዘዙ የኢህአፓ ቅሬቶችንና ምርኮኛ ወታደሮችን አሰባስቦ ኢህዴን (ኋላ ብአዴን) እና ኦህዴድ ብሎ በፈጠራቸውቡችሎቹ ኢህአዴግ ነኝ ብሎ በ‘ኢትዮጵያዊነት’ ለምድ ተሸፍኖ የመጣው ተኵላ ወያኔ፣ የአገሪቱን መንበረ መንግሥት ከያዘበት ጊዜጀምሮ አማራን አንገት አስደፍቶ ኢትዮጵያን እጥፋት አፋፍ አድርሷታል። ወያኔ በአማራና በሌሎች አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንእምቢታ ከመንበረ ሥልጣኑ ሲባረር፣ አባሪውና ተባባሪው የነበሩት ኦህዴድና ብአዴን “በደል ይረሳ፤ ፍቅርና ሰላም ይሁን” እያሉ”ብልጽግና” ነን ብለው በአማራው ላይ የታወጀውን የወያኔውን “ሕገመንግሥት” ማስፈጸም ቀጠሉ። እንደወያኔው በአማራ ጥላቻየናወዘውን ኦነግን እስከትጥቁ አስገብተውና ‘ኦሮሚያ’ በሚሉት ግዛት እንዲንሰራፋበት ፈቅደው ይኸው አማራውን ለማያባራ የዘርፍጅትና ለስደት ዳርገውታል።

ከተጠመቀበት የአማራ ጥላቻ ጋር ያደለበውን ወታደራዊ ኃይልና ኢኮኖሚያዊ ሀብት እንደያዘ የትግራይን ግዛት ተቆጣጥሮ እንዳሻውእንዲሆን ሑር የተለቀቀው ወያኔ፣ እስከአሁን ድረስ መንግሥት አለን ብለው በተቀመጡ የዋሃን ዜጎች አማሮችና አፋሮች ላይ ኍልቆመሣፍርት የለለው መከራ እያወረደ ይገኛል።

ደግነቱ፣ ለብዙ ዘመናት የደረሰበት መከራ የመከረው አማራ እየተሰባሰበ ዛሬ ንዝረቱ ለዓለም የሚሰማ ንቅናቄ ፈጥሯል። ይህ ንቅናቄከወለዳቸው የአማራ ተስፋዎች አንዱ በአባት አደሩ ሥርዓትና ወኔ ከየመንደሩ እየተጠራራ የተደራጀው የፋኖ ሠራዊት ነው። ከጅምሩከአማራ ጠሉ ሥርዓት አርጋጆችና ጋሻ ጃግሬዎች የሚደርስባቸውን ማሳደድ አልፈው ጠንካራ ሀይልነታቸውን ያሳዩት የፋኖ ወጣቶችወያኔው አማራን ከወረረ ጊዜ ጀምሮ በቂ የስልጠና፣ የመሳሪያ፣ የአደረጃጀትና የአቅርቦት ድጋፍ በሌለበት ሁኔታ በጎንደር፣ በወሎናበሸዋ ግንባሮች ተሰማርተው ለወገን ደራሽነታቸውን አሳይተዋል። መንግሥት ‘በመደበኛ የጦር ኃይልና አደረጃጀት አልቻልኩትም፤ሁሉም ዜጋ አገሩን ያድን’ ብሎ በተደጋጋሚ የ”ክተት” ጥሪ ባሰማ ጊዜም በግንባር ቀደምነት የተሰለፈው ይኸው የአማራ ፋኖ ነው።

የቀድሞው “የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር” የዛሬው የኢትዮጵያ የጸጥታ እና የደህንነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተመስገንጥሩነህ ጥር 20፣ 2014 ፋኖ በጦርነቱ ወቅት ያደረገውን ተጋድሎና ህዝባቸውን እየጣሉ የፈረጠጡ የመንግሥት አስተዳድሪዎችንበመታደግ ጭምር ያሳየውን የወገን እና የአገር መከታነት በማኮሰስ “አንዳንዶቹ” እያሉ በማናጠል በዝርፊያ እንደተሰማሩ በመክሰስ“ህዝብ አስታግሱልን የሚል ሮሮ አሰምቶባቸዋል ... ሥርዓት የማስያዝ ሥራ ይሠራል” በማለት ለአማራው ምን እንደደገሱለትአመላክተዋል፤ “ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት ይሏታል” ነው ብሂሉ።

በአማራው ላይ የሚደርሰውን በደልና ጥቃት ያከፋው በገዛ ልጆቹ አስፈጻሚነት ለረዥም ጊዜ በመሳሪያ ገፈፋ የደረሰበት የመከላከያአቅም የማሳጣት ጥቃት ነው። ዛሬ በመከራ አልፈን የደረስንበትን የመደራጀትና ራስን የመጠበቅ አቅም ማስነጠቅ የለብንም። በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአማራ ማኅበራት እቶ ተመስገን ጥሩነህ በፋኖ ላይ የሰነዘሩትን ዛቻ አማራው በዋዛ እንዳይመለከተውናይህ ዛቻ በጠቅላላ የአማራን ንቅናቄ የማዳፈን ጥረት አካል መሆኑን ተገንዝቦ በጭንቅ ቀን ወገን የታደጉ ጀግኖች ፋኖዎችን እናመሪዎቹን እንዲጠብቅ በማሳሰብ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድገግ ከወገናችን ጋር እንደምንቆም እናረጋግጣለን።

በየዱር ገደሉ የምትዋደቁ ፋኖ ወንድሞቻችን እና አህቶቻችንም ሙሉ ድጋፋችን እንደማይለያችሁ እየገለጽን ትግላችሁንአጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪ እናቀርባለን።

በዚህ አጋጣሚ በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአማራ ማኅበራት ለመላው የአማራ ህዝብ የሚከተለውን አጭር መልእክት ማስተላለፍእንድወድዳለን፦ አሁን በወገናችንና በአገራችን ላይ ከሁሉም አግጣጫ ያንዣበበውን ጥፋት መጠን በበቂ ሁኔታ ተገንዝበነዋል።በእኛ አንጻር የተሰለፉት እንዴት እኛን አጥፍተው አገሪቱን በአምሳላቸው እንደሚሰሯት በትጋት እያቀዱና እየፈጸሙ ይገኛሉ። እኛምአጥፊዎቻችን የሚጥሉልንን ማዘናጊያ እያንጠለጠልን እርስ በርስ መነታረኩን ትተን ዘለቄታችንን በሚወስኑ ጉዳዮች የበለጠተሰባስበን በአንድነት እንምከር - ለተግባር ፋኖ አርአያ ይሁነን!

አንድ አማራ አንድ ፋኖ!

የአማራ ማኅብረት ኅብረት በሰሜን አሜሪካ/Federation of Amharas in North America (FANA)

በካናዳ የዐማራ ማኅበረሰብ ኅብረት (ካሳ)/Canadian Amhara Societies Alliance (CASA)

Is Amharic?
More To Read