ትህነግ እና ኦነግ አሁንኑ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ  አጥብቀን እንጠይቃለን

ትህነግ እና ኦነግ አሁንኑ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ  አጥብቀን እንጠይቃለን!!!

ማንነትን በለየ መልኩ በአማራዎች ላይ በደረሰው የጅምላ ጭፍጨፋና በሌሎች ኢትዮጲያን ወገኖቻችን ላይ የተደረገው የዘር ተኮር ግድያን አስመልክቶ የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን ለመግለፅ እንወዳለን። ከጊዜ ጊዜ  ማንነት እየነጠሉ ማሳደዱ እና መግደሉ ጭራሽ ተባብሶ በገለልተኝነት የሃገሩን ዳር ድንበር ለመጠበቅ ዘብ በቆመው መከላከያ ሰራዊት ድረስ ዘልቆ   አማራው አገር ድንበሩን እየጠበቀ ባለበት ሰአት በስራ ባልደረቦቹ አማራ በመሆኑ ብቻ እንዲረሽን ተደርጓል። ይህ በቃላት ሊገልጡት የማይቻል እጅግ አረመኔያዊ  የግፍ ግፍ  ነው።  በዚህ ዘመን በተለያዩ አገራችን ክፍል የሚኖረው አማራ  በማንነቱ እየተሳደደና እየታረደ ነው። ይባስ ብሎ አማራው የአገሩን ድንበር ለማስጠበቅ በተሰማራበት ሰአት በማንነቱ ምክያት በስራ ባልደርቦቹ በተኛበት በአሰቃቂ ሁኔታ ተረሽኗል።  ይህ የግፍ ጥግ እና ማለቂያ የሌለው እብሪት እየተፈጸመ ያለው ደግሞ እስከ  ሀገር መከላከያ ወስጥ ድረስ በዘለቀው  በትህነግ (ሕወሓት) እና በኦነግ አረመኔያዊ ትብብር እና የቅንጀት  እኩይ ስራ ነው። 

የአማራ ዘርን ከምድረ ገፅ ጨርሶ ለማጥፋት የተደረገው ሴራ የተቀናበረው ከ45 አመታት በላይ የፈጀ የውሸት ትርክት እና ጥላቻን በህዝብ ላይ በማስረጽ፣ ኢትዮጲያውያን ያልተስማሙበት እና ያላፀደቁት ከፋፋይ ህገመንግስት በመጫን እንዲሁም  በታሪክም፤ በአኗኗር ዘይቤም፤ በማህበራዊ መስተጋብርም በምጣኔ ሃብት አስተዳደርም፤ ምንም አይነት ስሜት የማይሰጡ ኢትዮጲያን በነገድ ከፋፍለው ለመመዝበር በሚመች በኩል ብቻ የ“ብሔር ፌደራሊዝም”ን ተከትለው የተዋቀሩ  ክልሎችን በመጠቀም ሲሆን ችግሩ ጨርሶ እንዲፈታ እነዚህ ሁሉ ነገሮች መፍትሔ ሊሰጣቸው ያስገድዳል።  ነገር ግን እነዚህን ሁሉ የአማራውን ዘር ለማጥፋት እንዲሁም ኢትዮጲያውያንን ከፋፍሎ ዘላለም እየመዘበሩ ለመግዛት የቀረቡትን ዜዴዎች የቀረፁት፤ እነዚሁንም ተጠቅመው እስካሁን ድረስ አማራውን በመጨፍጨፍ ላይ የሚገኙት የህውሃት እና የኦነግ ድርጅቶች ያለምንም መታቀብ፣ እንደልብ እየተዘዋወሩ መንቀሳቀስ አሁን እየተደረገ ላለው ጭፍጨፋ ግምባር ቀደም ምክናያት ነው! አማራው በየእለቱ በመቶዎች እና በሽዎች የሚቆጠር አስከሬን ስብሳቢ መሆኑ ዛሬውኑ መቆም አለበት። ለዚህም እንደግምባር ቀደም መፍትሔ ትህነግ (ሕወሓት)  እና ኦነግ አሁኑኑ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ  አጥብቀን እንጠይቃለን!!! 

  ሰለሆነም፦ 

1) የተከበርከው የአማራ ህዝብ ሆይ፦  ትህነግ(ሕወሓት)ን ለፍርድ  ለማቅረብ የሚደረገውን መራር  ትግል አጠናክረህ እንድትቀጥል እናሳስባለን።  የዐማራ ህዝብ ደምህን ለነፃነትህ እየተዋደቁ ላሉ ከመለገስ ጀምሮ ለፍትህ እና ሰብዓዊ አላማ በመሰለፍህ እናደንቅሃለን እናመሰግናለን።  የህውሃትን አረመኔያዊ ጭካኔ ቀድመህ ተረድተህ፤ ህውሃት ጦርነት ከገባ ቢቀናውም ባይቀናውም፤ ከዚህ በፊት በሃይል ከጎንደር እና ከወሎ የወሰዳቸው ሁመራ፤ ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምት፤ ራያ ላይ ያሉ አማራዎችን ከከፋ ጭፍጨፋ ለማዳን  በፋኖ፤ በሚሊሻ እና በልዩ ሃይል በኩል ተሰልፈህ  ህይወትህን ሰጥተህ ለፈፀምከው ሰብዓዊ ጀብዱ ፤ከዚያም አልፈህ  የመከላያ ሰራዊትን ህይወት እስከመታደግ ድረስ የምታደርገውን ተጋድሎ በእጅጉ እናደንቃለን። ያለመዘናጋት ህውሃት ጦርነት እንደከፈት ሲታወቅ በፍጥነት ደጀንነቱን ብትጀምር እንኳን፤ በማይካድራ ሁመራ የወገን ጦር ገስግሶ ሳይደርስ በፊት በምን አይነት አሰቃቂ ሁኔታ ከ500 በላይ ንፁሃንን ህውሃት አሁንም አጥፍቶ እንደሄደ የአለም ህዝብ ያየው ነው። ወገን ሆይ፤ ከዚህ በኋላ ጉዳዩ የርስትና የታሪክ እንዲሁም የህውሃትን በደል የመዘገብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በግልጽ የሰብዓዊነት ጥያቄ ሆኗል! እነዚህ ለዘመናት መከራና ስቃይ የታየባቸው አስተዳደሮች ከእንግዲህ በኋላ ለሰዓታት ወደ ፋሺስት ህውሃት አገዛዝ ሊመለሱ አይገባም፤ ወደትክክለኛው ታሪካዊ አስተዳደራዊ ተዋረዳቸው ወደ ጎንደር እና ወሎ እንዲመለሱ ጠንክረህ ታገል።    በተመሳሳይም  ለህልውናህ የዘወትር አደጋ የሆኑት  ትህነግ  እና ግብረ አበሩን ኦነግን በሽብርተኝነት እንዲከሰሱ አምርረህ እንድትጠይቅ እናሳስባለን። 


2) የተከበርከው የኢትዮዽያ ህዝብ ሆይ፥ ትህነግ(ሕወሓት) ላለፉት ሶስት አስርት አመታት የአገራችን ከፋፍሎና ሸንሽኖ ከሰውነት ጎራ አውጥቶ እርስ በርሳችን እንድንባላና የአውሬነት አሳቤ እንድላበስ አድርጎን ቆይቷል።  እስካሁን ባደረከው መራር ትግል ትህነግ(ሕወሓት) ከስልጣን ወርዶ ኢትዮዽያንም አብሬ ይዤ ካልሞትኩ እያለ እየተንፈራገጠ ይገኛል። ስለሆንም ትህነግ መካነ መቃብር እስኪገባ ድረስና ርዝራዦቹም ለፍርድ  እንዲቀርቡ የእስካሁኑ ትግልህን ያለመዘናጋት ቀጥል። በተጨማሪም ማለቂያ ያጣውን የወገናችን የዐማራ ህዝብን እልቂት መርዶ አስተጋቢዎች መሆናችንን ስናሰብ ጥልቅ ሃዘን ይሰማናል።ነገር ግን የዐማራ ህዝብ ግፍ ሞልቶ ስለተረፈ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ግልጽ እና አጭር ጥያቄ እናቀርባለን።  የዐማራ ህዝብ ግፍና በደል ተሰምቷችሁ የመጨረሻ ጥሪያችንን ተቀብላችሁ አብራችሁን እንድትቆሙ እና ትህነግ እና ኦነግን በሽብርተኝነት እዲፈረጅ እና ለፍርድ እንዲቀርቡ አሁኑኑ  ድምጻችሁን እንድታሰሙ እንጠይቃለን::  

3. ለተከበርከው ወንድም የትግራይ ህዝብ፦ ከማህፀንህ የበቀለው ትህነግ/ሕወሓት የተባለው  የጥፋት ቡድን በዐማራ ህዝብ ላይ እስከ አሁን ያደረሰውን እና አሁንም እያደረስ ያለውን እልቂት ለአንተ ማስረዳት ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብናል። ነገር ግን በጥላቻ የታወረውን የትህነግ/ሕወሓት የጥፋት ስብስብ ብቻ ሳይሆን በገንዘብ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ተደለሎ የትህነግን የጥፋት መንገድ እየተከተለ እኩይ አላማውን የሚያስፈፅሙለትን እና አስተሳሰቡን የሚጋሩትን  የትህነግ ተላላኪዎች  በሙሉ  መንጥረህ ከውስጥህ አውጥተህ ለፍርድ እንደታቀርብ ጥሪ እናደርጋለን። ዐማራም ይሁን  ትግራይም እንደ ህዝብ ለዘለቂታው የሚኖሩ ናቸው:: ነገር ግን በስምህ የግፍ ግፍ እየፈፅመ ያለውን ጊዜያዊ እና ክፉ ጥገኛ የሆነብህን ተህዋስ ያለምንም  ርህራሄ አሳልፈህ ለፍትህ እንድትሰጥ እና ከወንድም ዐማራ ህዝብ ጋር በአንድነት እንደትቆም  ጥሪ እናቀርባለን። ሆኖም ይህን ሳታደርግ ከቀረህ ግን ታሪክ የሚፋረድህ ይሆናል። 

5. ለአፍሪካ ህብረት እና ለመላው ዓለም ይህንን ማንነት እየለየ ከመግደልና ከማሳደድ አልፎ ዘርን ጨርሶ እስከማጥፋት እየሄዱ ያሉትን ትህነግ እና ኦነግ የተባሉ ድርጅቶችን በትክክለኛ ግብራቸው በአሽባሪነት እንዲፈረጁ  የምናደርገውን ጥረት እንድትደግፉልን  በአጽንዖት እንጠይቃለን። ይህንን አሁኑኑ ባታደርጉ ግን ሩዋንዳ ላይ የደረሰውን ጥፋት መታደግ ስትችሉ በቸልተኝነት  አይታችሁ እንዳላየ በማለፋችሁ የደረሰው የከፋ ጉዳት አሁንም እንዲደገም እየፈቀዳችሁ መሆኑ ይታወቅልን። 

አሁንም በድጋሚ  ትህነግ(ሕወሓት) እና ኦነግ አሁንኑ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ  አጥብቀን እንጠይቃለን!!!

ፍትህ በየቀኑ  የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመበት ላለው ለወገናችን የዐማራ ህዝብ። ክብር ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ይሁን:: 

 

 

የዐማራ ባለሙያዎች ማህበር( ዐምባ)                   

ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ

ህዳር 3 2013 ዓ.ም.

 

Is Amharic?
More To Read