እንቆቅልሽ

እንቆቅልሽ

በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ እዉቅና ያተረፉትን እስረኞች ብቻ ለቆ በተመሳሳይ ክስ ምንም በማያዉቁት የታሰሩትን ወንድሞቻችንን ወደ ከፋ የጨለማ ቤት አዉርዶ ማሰቃየት ምን ይባላል? በዶ/ር አብይ የሚመራዉ የኢትዮጵያ መንግስት እስረኞችን ከጎረቤት ሀገር ድረስ ተደራድሮ ማስመለሱ የሚታወስ ሲሆን፦ ወንድሞቻችን በጨለማ ሲሰቃዩ እየሰማ እያየ ለምን ዝም አለ? ለዉጡ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ማማለል ወይስ እዉነተኛ ለሀገርና ለህዝብ የታሰበ ለዉጥ ነዉ? የአማራ ህዝብ አሁንም ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉት። ህዝቡ ጥያቄዎቹ ሳይመለሱ ይህ ሁሉ ስቃይ አሁንም እየደረሰበትና እየተመለከተ ከኖረበት ቀየዉ እየተሰደደና አሁንም እየተገደለ በምን መስፈርት ነዉ በደፈናዉ በጭፍኑ የመጣዉን ለዉጥ ሆ ግር ብለህ ተከተል ሊባል የሚችለዉ? እንቆቅልሽ ነዉ እንቆቅልሽ!

የልጄን ዐይን አይቼ ብሞት ጥሩ ነበር” - ልጃቸው የታሰረባቸው 82 ዓመት አባት
#Ethiopia #Amhara #VOAAmharic
በሽብር ወንጀል ተከሶ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘው የጎንደር ዩኒቨርስቲ መምሕር ጌታ አስራደ ከእስር እንዲፈታ ቤተሰቦቹ ተማፀኑ። ሌሎች እስረኞች በይቅርታና በምሕረት እየተለቀቁ በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱ እስረኞች ግን አሁንም ድረስ ጭለማ ቤት ውስጥ ተዘግቶባቸው ይገኛሉ ብለዋል። (ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ)

https://bit.ly/2sahIVI