ከአማራ ድርጅቶች እና ማህበራት ስብስብ(አድማስ) የተሰጠ መግለጫ
መጋቢት 18, 2010
በትግሬ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር(ትሕነግ) የሚመራው ዘረኛና ከፋፋይ፣ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ የሆነው ድርጅት የሚመራው ኢሕአዴግ ፣በ27 ዓመታት አረመኔአዊ አገዛዝ በአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም፣ ግዛታዊ አንድነት፣ በሕዝቡ አብሮነት ስሜት ላይ የፈጸማቸው አፍርሽ ተግባሮች ኢትዮጵያን እንደ አገር ልትቀጥል ወደ ማትችልበት አደገኛ አዘቅት ውስጥ እየከተታት እንዳለ ይታወቃል። ከዚህ አስከፊ የመበታተን እና የእርስ በርስ እልቂት መውጣት እንዲቻል፣ ዜጎች በዜግነታቸው፣ የፖለቲካ፣ የሲቪክ፣ የሙያ ማኅበራትና የብዙኃን መገናኛዎች አገሪቱና ሕዝቡ ከአስከፊ ጥፋት ራሳቸውን መከላከል እንዲችሉ በየፊናቸው የተቻላቸውን ሲያስተምሩና ሲመክሩ የነበሩና ያሉ ግለሰቦችን ከመግደልና ከማሰደድ የተረፉትን በሀሰት ክስ ወንጅሎ ለበርካታ ዓመታት አስሮ ማሰቃየቱ ይታወቃል።